አርነት በምርኮ ውስጥ ላሉት ከእስልምና ቀንበር ለመላቀቅ የሚያስችሉ ለየት ያሉ ሐሳቦችን ያቀርባል፡፡ 'የእግዚአብሔርን ልጆች የከበረ ነጻነት' ለመቀዳጀት (ሮሜ 8፡21) የመስቀሉን ኃይል መለማመድ የሚያስችሉ ተግባራዊ ቁልፎችን ይዟል፡፡
የተጠቀሱት ጸሎቶችና አዋጆች በስድስቱም አህጉራት በተግባር የተፈተኑ ናቸው፡፡ ሰዎችን ከእስራት ነፃ የማውጣት፣ ትውልድን የያዙትን ብርቱ ኃይላት የማስለቀቅ እንዲሁም ሰዎች የክርስቶስን የማዳን ኃይል ድፍረትን በተሞላና ውጤታማ በሆነ መንገድ መመስከር ይችሉ ዘንድ የማገዝ ፋይዳቸው የተረጋገጠ ነው፡፡